የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ ተጀመረ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 83 ሺሕ 500 ብር መሆኑም ምክር ቤቱ ባወጣው የዋጋ ዝርዝር ተመላክቷል።

ምክር ቤቱ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው ባንክ እና ቁጥሮቻቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ኦርጅናሉን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበትም ነው ያስታወቀው።

የሐጅ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችም እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡፡
1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ
2. የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ
3. የታደሰ ፓስፖርት ያለው፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ኃይሎች ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል።

4. ባልና ሚስት አብረው የሚሄዱ ከሆነ የጋብቻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል። ግዴታ ነው!
5. ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገብ ሂደቱን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚቻል ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW