የሕወሓት ከ6 ክፍለ ጦር በላይ ታጣቂ ኃይል ተደመሰሰ

ነሐሴ 26/2013 (ዋልታ) – በደባርቅ ጥቃት ለመፈጸም የህወሓት ቡድን አስገድዶ ያሰለፈው ከ6 ክፍለ ጦር በላይ ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በፌስቡክ ገፁ ወራሪው ኃይል በገባበት ስፍራ መደምሰሱን አሳውቋል፡፡

አሸባሪው ሕወሓት በደባርቅ ወረዳ ቦዛ አካባቢን በማለፍ የዳባት ወረዳ ዲያ የሚባል የሸለቆ መንገድ ተከትሎ ጭና የተባለ ቀበሌ አድርጎ የወቅን ተራራንና መሰል የተያያዙ ሰንሰለታማ ኮረብታወችን ተቆጣጥሬ ደባርቅን እይዛለሁ ከዛም ጎንደርን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችለኛል ብሎ ያቀደው እቅድ ለተከታታይ 30 ስዓታት በተካሄደ ውጊያ ከሽፏል፡፡

በውጊያው መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ የዳባትና ደባርቅ ወጣትና ህዝብ በጋራ ብርቱ ክንዳቸውን አሳርፈውበታል።

ቀጣይ አስገድዶ ለሚያቀርበው ሃይልም ልኩን እንደሚሰጠው እና ቀጣይ የተወረሩ ቦታወችን ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ህዝባችን፣ ሚሊሻችንና ልዩ ሃይላችን ፋኖ ከጀግናው መከላከያችን ጋር በመቀናጀት አኩሪ ገድል ለመፈፀም በመገስገስ ላይ ይገኛሉ።