የሕወሓት የሽብር ቡድን ከሰማይ በታች ሁሉንም አይነት ግፎችን ፈፅሟል- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የሕወሓት የሽብር ቡድን ከሰማይ በታች ሁሉንም አይነት ግፎችን በዜጎች ላይ መፈጸሙን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 27 ሚሊየን ብር ለህልውና ዘመቻው የሚውል ድጋፍ አድርጓል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የሕወሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያልፈፀመው ግፍ እና ሰቆቃ የለም ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የሽቡር ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ሴቶችን ደፍሯል፣ የግልና የመንግስት ንብረቶችን አውድሟል ብለዋል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን በአሁኑ ወቅት ሰሞኑን የቅማንት ፅንፈኛ ቡድን ጋር በመተባበር በመተማ የከፈተውን ግንባር ጨምሮ በ 5 ግንባሮች ጦርነት ከፍቶብናል ነው ያሉት፡፡

ይህንን የሽብር ቡድን ለመደምሰሰ ደግሞ ሁሉም አቅሙ የፈቀደውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለህልውና ዘመቻው ላደረገው ድጋፍ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እንደ ኢብኮ ዘገባ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባሕር-ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ልንገረው የልማት ባንክ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡