የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራው ነው – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እና የርዕሠ መስተደድር ፅሕፈት ቤት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እገመገመ ነው።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤትና የርዕሠ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ደረሰ ገቲሳ ፣ በየደረጃው ከሕዝብ የሚነሱ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የአሰራር ማዕቀፉን ተከትሎ መፈጸምና ሌላውን መደገፍ ትኩረት የሚሹ ተግባራት መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው፣ በሁሉም የሥራ መስክ ዕቅድ አቅዶ በመምራት ተግባራትን በየወቅቱ እየገመገሙ ሥራዎችን ማሳለጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የሁሉም ዞኖች አስተዳደር የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የቀሪ ወራት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!