የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተሩ ሀሰተኛ መረጃን መዋጋት ላይ ትኩረት ያስፈልጋል አሉ

                                          የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው 

ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) ሀሰተኛ መረጃ አደገኛ መርዝ ነው፤ ግለሰብን ብቻ ሳይሆን አገርን የማጥፋት ከፍተኛ አቅም አለው ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ተናገሩ፡፡

የአዲስ ወግ አንድ ጉዳይ ውይይት ‹‹የኅልውና ጥሪ እና አገርን የማዳን ርብርብ›› በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህም የውይይት መድረክ ኮሚሽነር እንደሻው  ‹‹በአገራችን እየተፈጸመ ያለው ወንጀል እና የትከፈተብን ዘመቻ ዘርፍ ብዙ ከመሆኑም በላይ ለበርካታ ዓመታት ታቅዶ እና በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥ ካሉ ሽብርተኞች እና የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማይፈልጉ ከውጭ ኃይሎች በቅንጅት እየተፈጸመ ያለ ነው›› ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር እንደሻው ዓለም ዐቀፍ የመገናኛ ተቋማት በተሳሳተ መረጃ ኢትዮጵያዊያን የሚያደርጉትን የኅልውና ዘመቻ ለማኮልሸት የሀሰት መረጃዎችን በማበስራጨት ተግባር ላይ መሰማራታቸውን አንስተዋል፡፡

ይህንንም ተጽዕኖ በእስተማማኝ ሁኔታ ለመመከት 3 ጉዳዮች ላይ መስራት ይኖርብናል ያሉት ኮሚሽነሩ እነዚህም ሰፊውን ሕዝብ፣ ወዳጅ አገራትንና በሀሰት መረጃ ስርጭት ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡