የመስቀል እና እሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚያስችል ዉይይት እየተካሄደ ነዉ

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የ2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራና የእሬቻ ክብረ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቅ እንዲችሉ ከሚመለከታቸዉ አካላትና የከተማዋ ወጣቶች ጋር ምክክር እያካሄደ ነዉ።

በዓላቱ ሲከበሩ ሽብርተኞች እና ፀረ ሰላም ሀይሎች የሀይማኖት ተቋማትን እና በዓላትን ሽፋን አድርገዉ እንዳይንቀሳቀሱ የፀጥታና የሰላሙን ሁኔታ ማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተገልፆል።

በዓላቱ በሰላም ተከብረዉ እንዲጠናቀቁ የፀጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮችና ቦታዎችን በመለየት የተጠናከረ ጥበቃ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ሁሉም በየደረጃዉ በመቀናጀት እንዲሰራ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር በየደረጃዉ የህዝብ ዉይይት እንደሚካሄድ እና በአጠቃላይ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሀላፊነቱን እንዲወጣ 100 ሺሕ ሰዉ በዉይይቱ እንደሚሳተፍም ታዉቋል።

በህይወት አክሊሉ