ግንቦት 03/2013 (ዋልታ) – በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ታጣቂዎች የተሐድሶ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ።
በስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት እና የክልሉ አመራሮች ተግኝተዋል።
ለ15 ቀናት የሚሰጠው የተሐድሶ ስልጠና ታጣቂዎች ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ ግንዛቤያቸውን በማስፋት ለአገርና ለአካባቢያቸው ጠቃሚ ዜጋ የሆነው እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ ነው።
በሥራ ፈጠራ ላይ ክህሎታቸውን ማሳደግ ሌላው የስልጠናው ዓላማ ሲሆን በሥነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ ማስቻልም የስልጠናው ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።
(ምንጭ፡- ኢዜአ)