“የኢትዮጵያዊያን ልዩ የድል ብስራት ቀን ነው” – ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ

የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት

ሐምሌ 12/2013 (ዋልታ) – የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የታላቁ ህዳሴ ገድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልከተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊትጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው የግድቡ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያን ህዝብ አንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

“የግድቡ ውሃ ሙሌት አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ትብብር ሰርተዋል”ያሉት ጀነራል ብርሃኑ፤ ግድቡ የሞላበት የዛሬው እለት “የኢትዮጵያዊያን ልዩ የድል ብስራት ቀን ነው” ብለዋል።

የህዳሴ ግድብ ፕሮጄክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ይግዛው፣ የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፣ የትራስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የእንኳን ደስ አላችሁ መልክዕት አስተላልፈዋል፡

የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ባስተላለፉት እንኳን ደስ ያለን መልዕክት ዓባይ ሀገር ሆነ፣ ለሀገር ሆነ፣ ለአህጉር ሆነ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዓባይ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት አስተሳሳሪ ገመድ፤ የሰላም፣ የአብሮ የመልማትና የማደግ አገናኝ ድልድይ ለመሆን ቃሉን አድሷል ያሉት ሚኒስትሯ፣ የዓባይን ህልም ለመፍታት ለወጣችሁ ለወረዳችሁ የሀገሬ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች መላው ኢትዮጵያውያን ምስጋናዬን አቀርባለው ብለዋል፡:

የህዳሴ ግድብ ፕሮጄክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ይግዛው፣ የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፣ የትራስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የእንኳን ደስ አላችሁ መልክዕት አስተላልፈዋል፡፡

የውጭ ግንኙነት ስትራቴጅካዊ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ቧያለው በበኩላቸው፣ “ዓባይ ወንዝ ነበር፣ ተገርቶ ወንዝም ሀይቅም ሆነ፣ ከእንግዲህ በወንዝነቱ ይፈሳል፣ በሀይቅነቱ ኢትዮጵያ ለፈለገችው ልማት ሁሉ ለማዋል እጅ ሰጥቷል” ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳች አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌትን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ያሰፈሩን ጽሑፍ ጠቅሰው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

16:5