የመኖሪያ ቤት አከራይ የተከራዩን ሙሉ መረጃ በመያዝ ማስመዝገብ እንዳለበት ተገለጸ

ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የተከራዩን መሉ መረጃ በመያዝ በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የፀጥታ ሥራውን የሚደግፉ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ መመሪያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተከራዩን ማንነት የሚገልፅ ማስረጃ በመያዝ በአሥራ አንዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያዎች እና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወሰድ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡