የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሦስት ወራት ተራዘመ

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ደንቡም ላለፉት ሦስት ወራትም እንዲራዘም ተደርጎ አንደነበርም ይታወሳል፡፡

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህላልን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ እንድንሻገር የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW