የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ አባላት የማዕረግ ዕድገት

የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት

መስከረም 7/2014 (ዋልታ) በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል፡፡

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የፋናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተር እና የዋና መምሪያው ተወካይ ብ/ጄ ደረጀ መገርሳ ባስተላለፉት መልክት መንግስት በሃገሪቱ ህልውና ላይ የተደቀነውን ፈተና በመቀልበስ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር እየሰራ ባለበት በአሁኑ ጊዜም ሳይቀር በሠራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሠራዊቱን መብት ለማክበር ትኩረት በመስጠት በተለየ ሁኔታ ወስኖ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ስማቸው አናጋው በበኩላቸው፣ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ተሳትፈው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ (በልዩ ሁኔታ) እና የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ 150 የዋና መምሪያው አባላት በሚመለከተው አካል ፀድቆ ከምክትል አስር አለቃ እስከ ሙሉ ኮሎኔል የሚደርስ የማእረግ እድገት መሰጠቱን መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡