ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደው 25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ማራቶን ሬሌ ውድድር የመከላከያ አትሌቲክስ ቡድን አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በውድድሩም ሀገራቸውን ወክለው ድልን ያስመዘገቡ አትሌቶች ጌታነህ ሞላ፣ ገበያነሽ አየለ እና ሌሎችም ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፈዋል።
የዋንጫ ሽልማት ሥነሥርዓት የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ የመከላከያ ስፖርት ክለብ ለሀገሪቱ ስፖርት ደማቅ ታሪክና ሁለንተናዊ ዕድገት የማይተካ ሚና በመጫወት ግምባር ቀደም መሆኑን ተጠቁሟል።
(ምንጭ፡-የመከላከያ ሚኒስቴር)