የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የመጀመሪያ ዙር ምሩቃንን አስመረቀ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የመጀመሪያ ዙር ምሩቃንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡

ኮሌጁ በአንድነት ፓርክ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን ያካሄደ ሲሆን በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ፣ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

ምርቃቱን አስመልክተው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ የዛሬው ምረቃ ለነገ ዕውቀትን ፍለጋ ሊያዘጋጃችሁ ያስፈልጋል ብለዋል።

“ዕውቀትን ሳትታክቱና ሳታቋርጡ እንድትሹ፣ ያገኛችሁትን ዕውቀት እንድታካፍሉ አደራ እላችኋለሁ”ም ሲሉ ለተመራቂዎች ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 38 ሙያተኞችን አሰልጥኖ ዛሬ አስመርቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW