የመደመር መንገድ መጽሐፍ ሁለት ዓላማ አንግቧል- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – የመደመር መንገድ መጽሐፍ ሁለት ዓላማ ያነገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ይህም በአንድ በኩል ሐሳብ ማስተላለፍ በሌላ በኩል በገቢው ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የመጽሐፉ የነጠላ መሸጫ ዋጋ 350 ብር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አንባቢዎች ሊዳረስ የሚችል በቂ ቅጅ ስላለ ከዚህ በላይ ከሚሸጡት እንዳይገዙም አሳስበዋል፡፡