የመዲናዋ ትምህርት ቤቶች በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በከተማ መስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ያሰባሰበውን 100 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አስረክቧል።

በድጋፉ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና የመማሪያ ቁሳቁስ የተካተቱ ሲሆን በአፋር እና በደብረብርሃን ለሚገኙ በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ይውላል ተብሏል፡፡