የመጀመሪያው የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር አስተዳደር ቦርድ ተመሠረተ

ሐምሌ 22/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የፌደራል የጠበቆች ማኅበር አስተዳደር ቦርድ ተመሰረተ፡፡

በሕግ እና በሕግ ብቻ የሚመራ የጠበቆች ቦርድ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የፌደራል የጠበቆች ማኅበር አስተዳደር ቦርድ ሊመሰረት እንደቻለ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የፍትሕና የጥብቅና ስርዓትን ያዘምናል ተብሎ የታመነበት ቦርዱ ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስቴር ነው፡፡

የቦርዱ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ያካሄዱ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ቦርዱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ሁለት የጠበቆች የሙያ ማኅበራት ቢኖሩም በቦርድ ደረጃ ሲቋቋም ይህ የመጀመሪያ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።