የሚኒስቴሮች የ2014 አፈጻጸም ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባሉበት እየተገመገመ ነው

ግንቦት 29/2014 (ዋልታ) የሚኒስቴሮች የ2014 አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሉበት በአዋሽ እየተገመገመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመሩት በዚህ መድረክ ላይም የእያንዳንዱ ሚኒስቴር  ያለፉት ዘጠኝ  ወራት አፈጻጸም ቀርቦ እየተገመገመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፥ በዓመቱ ሀገሪቱ በውጫዊ እና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብታልፍም፣ ኢኮኖሚውን እንቅስቃሴው ሳይስተጓጎል ማስቀጠል ተችሏል ብለዋል።

ለዚህም የበጋ ስንዴ፣ የሸቀጦች ወጭ ንግድ፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት እንዲሁም የሕዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ በዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች ትልቅ ፋይዳ እንደነበራቸው ተናግረዋል።