ግንቦት 29/2013 (ዋልታ) – የሚኔሶታ ሚድዌስት የህዳሴ ግድብ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በ2ኛው ዙር ያሰባሰበውን 50 ሺህ ዶላር አስረክበዋል።
የኮሚቴው ሰብበሳቢ ቄስ ፍራንሲስ እስጢፋኖስ ለሁለተኛ ዙር 50 ሺህ ዶላር ቼክ ለግድቡ ግንባታ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ ጥቂት የቀረውን የፕሮጄክት ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አምባሳደር አብዱላዚዝ መሐመድ በበኩላቸው ኮሚቴው ከዚህ ቀደም 40 ሺህ ዶላር በቼክ በአምባሳደር ብርትኳን አያኖ በኩል ለግምባታው ማስረከባቸውን አስታውሰው፣ በድምሩ 90 ሺህ ዶላር የደገፉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አትዮጵያውያን እና ትውልደ አትዮጵያውያን ለሚያደርጓቸው ድጋፎች ሁሉ ምስጋና ማቅረባቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።