የማዕድን ሚኒስትሩ ከቱርክ ባለሃብቶች ጋር ለመወያየት ኢስታንቡል ገቡ

ግንቦት 22/2014 (ዋልታ) የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ለማድረግ ኢስታንቡል መግባታቸውን የማድድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገለፁ።

በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት አቅም ዙሪያ በሚያተኩር ውይይት ላይ ለመሳተፍ ኢስታንቡል የገቡት ሚኒስትሩ ወደዚያ ያቀኑት በቱርክ ሪፐብሊክ የንግድ ሚኒስትር መህመት ሙሽ ግብዣ መሰረት መሆኑን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢስታንቡል ሲደርሱ በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ አደም መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።