የማዕድን ሚኒስትር ለአፋር ክልል የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 9/2014 (ዋልታ) የማዕድን ሚኒስትር በአፋር ክልል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ ለፈረሱ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የማዕድን ሚኒስትር ታከል ኡማ ድጋፉ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የማዕድን ኩባንያዎች የተሰባሰበ መሆኑን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ታከል ኡማ “የአፋር ወንድምና እህቶቼ ትግል እና እየከፈሉ ያለው ዋጋ የቀደምት አባቶቻቸውን ገድል እና ጀግንነት ህያውነት በተግባር ያሳየ፣ የአዲሱን ትውልድም አይበገሬነት ያስመሰከረ ነው” ብለዋል፡፡