የምልምል ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ተካሄደ

ነሐሴ 07/2013(ዋልታ) – በመከላከያ ማሰልጠኛ ማእከል ለከተቱት ምልምል ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ተካሄደ።

የማሰልጠኛዎቹ ዋና አስተባባሪ ባደረጉት ንግግር ፣ ሀገራቸውን በዚህ ወሳኝ ወቅት ለማገልገል በራስ ተነሳሽነት ዘምተው ለመጡት ምልምል ወታደሮች ያላቸውን ክብርና አድናቆት ገልጸዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለህዝብ ሰላም ሲባል የተሰጠውን የተኩስ አቁም እንደፍርሃት በመቁጠርና በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ህጻናት ሳይቀር አለም አቀፍ ህግን በመጣስ ለጦርነት እየማገደ እንሚገኝም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህን አሸባሪ ቡድን ባነሰ ጊዜ በመደምሰስ የሃገራችንን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ በማሰልጠኛ ማእከሉ የሚሰጡትን ስልጠናዎች በወኔና በሞራል በመሰልጠን ለቀጣይ ግዳጅ መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።