የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም እየተካሄደ ነው

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ በቀጠናው ከሰራተኛ ፍሰት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት በምትመራው በዚህ ፎረም ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል እንደ አህጉርም ይሁን እንደ ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የስራ እድል ፈጠራና የሰራተኛ ፍሰት ፈተና መሆኑን አንስተው ቀጠናዊ ትስስሮችን ማጎልበት  እንደሚያስፈልግ አንስተዋል ።

መድረኩ በቀጠናው መደበኛ የሰራተኛ ፍሰት እንዲኖር የሚያስችል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ የሚቀርብበት ሲሆን ከ11 ሀገራት የተውጣጣ ቀጠናዊ  የክህሎት ልማትና የወጣቶች ስራ ስምሪት የቴክኒክ ቡድን  ይቋቋማልም ተብሏል።

በመስከረም ቸርነት