ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮናን ልታዘጋጅ ነው

ሚያዚያ 25/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ከ28 ዓመት በኋላ ልታዘጋጅ መሆኗ ተገለጸ፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የአዋቂዎች የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ከሚያዚያ 27 እሰከ 30 በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን በሻምፒዮናው ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 አገራት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ እንደምትሳፍ የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በዚህ የስፖርት ዘርፍ አህጉራዊ ውድድር ስታዘጋጅ ከ28 ዓመታት በኃላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱንም ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

ሚኪያስ ምትኩ