የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ በሀረር ተከፈተ

ሚያዝያ 30/2014 (ዋልታ) አምስት የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ በሀረር ከተማ ተከፈተ።
አውደ ርዕዩን የሀረሪ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪና የኢፌዴሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ከፍተውታል።
አውደ ርዕዩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን አጎራባች ክልሎቹ ይበልጥ ተቀራርበው የባህል ትውውቅ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።
የአውደ ርዕዩ አስተባባሪ ይማጅ ዘካሪያ ለዋልታ እንደተናገሩት አውደ ርዕዩ የተለያዩ ምርቶቻቸውን ለሚያሳዩ አምራቾች የገበያ ትስስር እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ዋልታ ያነጋገራቸው የአውደ ርዕዩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አውደ ርዕዩ የገበያ ትስስር ከመፍጠሩ ባሻገር ከአጎራባች ክልሎች ጋር የባህል ትውውቅ እንድናደርግና አንድነታችንን እንድናጠናክር የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሱራፌል መንግሥቴ (ከሀረር)