የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

ጳጉሜን 2/2016 (አዲስ ዋልታ) የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ ግብር በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም እየተከበረ ይገኛል።

“የምስራቁ ጮራ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነን” በሚል መሪ ሃሳብ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሐረሪ ክልል እና በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ሲከበር ቆይቷል።

በዓሉም የልማት ስራዎችን በመጎብኘት፣ ሙዝየምና የፎቶ ግራፍ ዓውደ ርዕይ ለእይታ በማቅረብ፣ የፕሮጀክት ስራዎችን በመመረቅ ሲከበር መቆየቱን ከመከላከያ ሠራዊት የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ፣ ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችና መኮንኖች ተገኝተዋል።