የምክር ቤቱ አባላት በበጋ መስኖ የለማ የሰንዴ ማሳን ጎበኙ

በበጋ መስኖ የለማ የሰንዴ ማሳ

መጋቢት 23/2014 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አባላት በበጋ መስኖ የለማ የሰንዴ ማሳን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ አማኒ ቀበሌ 30 ሄክታር የሰንዴ ማሳ በማልማት ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ የግብርና ሥራን የውሃ አማራጮች በመጠቀም መስራት ከተቻለ እንደ ክልልም ሆነ እንደ አገር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚቻል በመስክ ጉብኝቱ ላይ ገልፀዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በዘመነ መንገድ በመቃኘት የኦርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሻሻል በስድስቱም የክልሉ ዞኖች በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በመስክ ያዩትን ተሞክሮ ወደመጡበት ሲመለሱ ለሕዝቡ ለማስተዋወቅና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ምክር ቤት የሁለት ቀናት ጉባኤውን በ6 አጀንዳዎች ላይ በመመክር ጉባኤውን አጠናቋል።

አክሊሉ ሲራጅ (ከቦንጋ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW