የምክትል ከንቲባዋ ሃዘን መልዕክት

ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ

ነሐሴ 28/2013 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንጋፋዉ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ ‘‘ኢትዮጵያ ታላቅ የጥበብ ሰዉ ነዉ ያጣችው’’ ያሉ ሲሆን፣ በአንጋፋዉ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈተ ህይወት እጅጉን አዝኛለሁ’’ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክታውን አስተላልፈዋል።

’’ዓለማየሁ እሸቴ ለሚወዳት ኢትዮጵያ በጥበብ ስራዎቹ ብዙ ያደረገ ሃገር ወዳድ ባለሙያ ነበር’’ ሲሉም ገልጸዋል።

ምክትል ከንቲባዋ አክለውም ‘’በራሴና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ ልባዊ መፅናናትን እመኛለሁ’’ ብለዋል።