የምዕራብ አዲስ አበባ የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከእቅዱ በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

ሐምሌ 01/2013 (ዋልታ) – የምዕራብ አዲስ አበባ  የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከእቅዱ በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልጿል።

ፅ/ቤቱ  በ2013 በጀት አመት 7 ነጥብ 74 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ 8 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው ያስታወቀው፡፡

የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ወሮ ቃለ ህይወት መኮነን እንደአስታወቁት አፈፃፀሙ ከእቅድ በላይ 113 በመቶ  ነው፡፡

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ግብራቸውን ካሳወቁ  5ሺህ 500 ግብር ከፋዮች 700 የሚሆኑት ግብር ከፋዮች ሀሰተኛ ደረሰን ተጠቅመው ተግኝተዋል።

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የበጀት አመቱ ማጠቃለያና የ2014 ዓም ግብር ማሳወቂያ ዝግጅት ላይ የተገኙት በገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ሚኒስትር ዲኤታ ዘመዴ ተፈራ የግብር አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲሆን የግብር ሰብሰባቢ ባለሙያዎች እምቅ አቅም ከዛም ባለፈ ባለፉት አመታት የተሰሩ ስራዎችና ግብር ከፋዮችን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

የሀገር ውስጥ ገቢን የመሰብሰብ ሂደቱ  ከ100 ፐርሰንት በላይ መድረሱንም የታክስ  ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ቱሉ ተናግረዋል፡፡

የምዕራብ አዲስ አበባ  የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅራንጫፍ ፅ/ቤት   በ2014 በጀት ዐመት 10 ቢሊዮን ብር ለመስብሰብ በእቅድ ተይዟል።

ከሀምሌ አንድ ጀምሮ እስከ ጥቅምት ድረስ ግብር ከፋዮች ገቢያቸውን አሳውቀው ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

(በምንይሉ ደስይበለው)