የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአረንጓዴ አሻራ ልማት በንቃት መሳተፍ ይገባል

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአረንጓዴ አሻራ ልማት በንቃት መሳተፍ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በሀረሪ ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት ከተተከሉ ችግኞች መካከል 72 በመቶ የሚሆነው የጸደቀ ሲሆን የመጽደቅ ምጣኔውን ለማሳደግ በዚህ ዓመት ካለፉት ዓመታት ተሞክሮ በመውሰድ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዘንድሮው መርኃ ግብር የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎች በማዘጋጀት እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም አመት በሀረሪ ለመትከል ከታቀደው 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኝ ውስጥ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን የተለያዩ ፍራፍሬዎች ሲሆኑ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ይረዳናል ተብሏል፡፡