የምግብ ዕርዳታን የያዙ ተጨማሪ 63 የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደርሰዋል

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – ለሰብዓዊ ዕርዳታ ምግብ የያዙ ተጨማሪ 63 የጭነት መኪናዎች ትግራይ ክልል መቀሌ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የምግብ እርዳታ የያዙ 220 የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል ገብተው ዛሬ መቀሌ መድረሳቸውን ነው የተገለጸው ።
በዚህም መሠረትም ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም ከተገለጸው በተጨማሪ፣ የምግብ ዕርዳታን የያዙ 63 የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደርሰዋል።