የምግብ ዘይትን በድብቅ ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው አለአግባብ የምግብ ፍጆታዎችንና ሌሎች ጥሬ እቃዎችን የሚሸሽጉና የሚያሸሹ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር በትናንትናው እለት ግብርኃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን ገለጸ፡፡

በዚህም በትናንትናው እለት ለሊቱን ከአዲስ አበባ ለኅብረተሰቡ የሚውለውን የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦችን ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቋል፡፡

አሁንም ቢሆን ሆነ ብለው መንግሥትንና ኅብረተሰቡን ጫና ውስጥ ለመክተትና እና ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረትን በመፍጠር ሕዝቡን ለማስጨነቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ኃይሎች በመኖራቸው ኅብረተሰቡ በየአካባቢው ጥቆማዎችን ለመንግሥት አካላት እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ሰፊ ክትትል በማድረግ ህገወጦችን ለህግ እንደሚያቀርብ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡