የራሺያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ለም/ጠ/ሚ እና ው/ጉ/ሚ ደመቀ መኮንን አስተላለፉ

የራሺያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) የራሺያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ሚኒስትሩ መልዕክቱን ያስተላለፉት አቶ ደመቀ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ዳግም በመመረጣቸው መሆኑን በኢትዮጵያ ከራሺያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል የፖለቲካ፣ ንግድ ኢኮኖሚ እና የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራትና ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩም አመልክተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በምስራቅ አፍሪካ ብሎም በአፍሪካ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎትም ገልጸዋል፡፡