የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን የመወንጀልና የማዋረድ ሴራ ውጤት ነው – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

መስከረም 11/2015 (ዋልታ) የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ዙሪያ ያወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን የመወንጀልና የማዋረድ ሴራ ውጤት ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡

አምባሳደር ሬድዋን በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ሪፖርቱ ፖለቲካዊ ግብ ይዞ የተሰናዳ መሆኑንም ገልፀው ሪፖርቱን ያዘጋጀው አካልም ለፍላጎቱ ሽፋን መስጫ እና ኢትዮጵን ለማዋረድ ብሎ ያዘጋጀው እንዲሁም እርስ በርሱ የሚጣረስ አድሏዊ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሰው ውድመት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በትግራይ ክልል ከደረሰው ያነሰ ነው ሲል አይኔን ግንባር ያርገው ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡