ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።
ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ ለመካፈል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW