የሲቪል፣ ፖለቲካ እና መብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብትን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሶስተኛዉን ብሔራዊ የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ረቂቅ ሰነድን አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት እና ከሀይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የሶስተኛዉ የብሄራዊ የድርጊት መርሀ ግብር ተፈፃሚ ለማድረግ ያለፉት ሁለት የሰብዓዊ መብት ብሄራዊ የድርጊት መርሀ ግብር ሰነዶች በሚገባ መዳሰሳቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናግረዋል፡፡
በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የብሄራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ፅህፈት ቤት ኃላፊ መድሃኒት ታመነ በበኩላቸው፣ የመርሃ ግብሩ በሀገሪቱ የሰብዓዊ ግንዛቤ እንዲጎለብትና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ በተደራጀ፣ በተቀናጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ የበለጠ እንዲሻሻል ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በረቂቅ ሰነዱ የተካተቱ ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ከተሳታፊዎች ግብዓት መሰብሰቡን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡