የሲዳማ ክልል ለሀገር መከላከያ ከ45 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረ

ሐምሌ 24/2013  (ዋልታ) – የሲዳማ ክልል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀገርን ለመታደግ ለሚያደርገው ዘመቻ 30 ሚሊየን ብር በጥሬ ብር እና 15 ሚሊየን ብር ደግሞ በአይነት ድጋፍ በአጠቃላይ 45  ሚሊየን ብር የሚወጣ ከመላው የሲዳማ ክልል ህዝብ የተወጣጣ ቁሳቁስ  በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

የመከላከያ ሚኒስቴር የህብረት ሎጂስቲክ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ስራ አመራርዳ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው የሲዳማ ክልል ለሀገር መከላከያ እያደረገያለውን ድጋፍ አመስግነው በአንድነት የጁንታውን ሀይል ዳግም እንዳሰራራ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል የብልፅግና ፖርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤሊያስ በበኩላቸው  ለሀገር መከላከያ የሚውለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚሆን ከ221 በላይ በሬዎች እንዲሁም 204 ፍየልና መሰል የአይነት ድጋፍ በክልል የሚገኙ  ከአመራሮ ባለ ሀብቶች በአጠቃላይ ከመላው ከክልሉ ነዋሪ የተሰበሰበ መሆኑን አንስተዋል።

(በዙፋን አምባቸው)