የሲዳማ ክልል ለመራጀት መራራ ትግል አድርጓል – ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌንዳሞ

 

ሀዋሳ፣ የካቲት 15 /2013 (ዋልታ) – የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልላዊ መንግስት የሆነበትን ክብረ በዓል የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የአ/አ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አበቤን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች በተገኙበት እየተከበረ ገኛል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ደረጉት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌንዳሞ በለዉጡ አመራር ህገመንግስታዊ ምላሽ ተገኝቷል ሲሉ የእንኳን ደስ ያለን መልዕት አስተላልፈዋል፡፡ ክልሉ የህብረ ብሔራዊ ማሳያ ተደርጎ ሊወሠድ ይችላል ብለዋል፡፡

ለለዉጡ አመራር ለጠ/ሚ አብይ አህመድ አክብሮት አለን ያሉት አቶ ደስታ ለአጋር ክልሎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የሲዳማ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በጋራ የሚኖር የአብሮነት ነፀብራቅ ነዉ ሲሉም ተደምጥዋል፡፡

ክልሉ የተሻለ ልማት እንዲያገኝ ቅድሚያ የሚሠጣቸዉን ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ፣ ክልሉ ለንግድና ኢንቨስትመንት ዝግጅት አድርጎ እየጠበቀ ነዉም ብለዋል፡፡

ክልሉ አዲስ ክልል እንደመሆኑ የሀብት ዉስንነት ስላለበት የክልል መንግስታት እና ባለሀብቶች የቻሉትን ድጋፍ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠይቀዋል፡፡
(በሰለሞን በየነ)