የሲዳማ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል

ሚያዚያ 22/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የሥራ ዘመን፣ 2ኛ ዙር 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ እንደሚጀምር አስታወቀ።
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሠ መሥተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።
እንዲሁም ምክር ቤቱ በሚቀርብለት ሹመት፣ በጀትና የተለያዩ አዋጆች ላይ ተወያይቶ የሚያፀድቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ጉባኤው ሌሎችም አጀንዳዎች እንደሚኖሩት የተናገሩት አፈ-ጉባኤዋ፤ በክልላዊና ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።