ጥቀምት 13/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር የሴት አመራሮች ቡድን (ኮከስ) ተመሰረተ።
በትምህርት ልማት ዘርፍ ተወዳዳሪና አምራች ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረትና ርብርብ ውስጥ የሴት መምህራን ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን በምስረታው ላይ የተገኙት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሯ ለትምህርት ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የዜጎችን የትምህርት ፍላጎትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡