የሴኔጋል ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም 23/2014 (ዋልታ) የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ኢትዮጵያ የምታካሂደውን በዓለ ሲመት ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በነገው ዕለት ለሚካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ የተለየዩ ሀገራት መሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

በመስከረም ቸርነት