የሴካፋ ውድድር በሁለት ሳምንት ተራዘመ

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ውድድር (ሴካፋ) በሁለት ሳምንት መራዘሙን አስታወቀ፡፡
ውድድሩ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀምር መገለጹን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፌዴሬሽኑ ውሳኔው የሴካፋ መሆኑን ገልፆ ከውድድሩ መጀመር ሶስት ቀናት በፊት ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እንደሚጀምሩም አስታውቋል።