የሶማሊያው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀቁ

መስከረም 20/2015 (ዋልታ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የሁለቱ አገራት መሪዎች የጋራ ስምምነትን ይፋ አድርጓል።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከከፍተኛ ልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በቆይታቸው በቀጠናዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች መክረዋል።

መሪዎቹ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ማድረጋቸው እንዲሁም የሽብርተኝነት እና የፅንፈኝነት ስጋትን ለማጥፋት እና በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲደርሱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል እንደተደረገላቸው ይታወሳል።