የሶማሌ ክልል ካቢኔ አባላት ለድርቅ ምላሽ 20 ሚሊዮን ብር ሊለግሱ ነው

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል የድርቅ ምላሽ ኮሚቴ ለድርቁ እየተሰጠ ያለው ምላሽ ያለበትን ደረጃ ገመገመ።
ግምገማውን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ የሚመራው ዐቢይ ኮሚቴ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ የድርቁን ምላሽ በቀጥታ የሚመራ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ አዋቅሯል።
የክልሉ ካቢኔ አባላትና የመንግሥት ተሿሚዎች ከወርሃዊ ደመወዛቸው ለድርቁ ምላሽ የሚውል 20 ሚሊዮን ብር እንደሚለግሱ መገለፁን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።