የሶማሌ ክልል የክልሉ ተወላጅ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር አመታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል መንግሥት ከክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት ጋር የሚያካሄደውን የጋራ አመታዊ ጉባዔ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በምክክሩ ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሁሴን ሃሺ ቃሲም (ፒኤችዲ) እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጠይብ አህመድ-ኑርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት፣ ባላሃብቶች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በየዓመቱ አንዴ በሚካሄደውን በዚሀ የጋራ ጉባኤ የክልሉ ዲያስፖራዎች መንግስት በክልሉ እያከናወነ ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የመሰረተ ልማት፣ የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ እና ዘርፈ ብዙ የክልሉ ሥራዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በሰፊው ይወያዩበታል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የዲያስፖራ አባለትና ባለሀብቶች በክልሉ እየተካሄደ በሚገኘው የኢንቨስትመንት እና ልማት ሥራዎች በተለይም በኢንዱስትሪ መሰረተ ልማት ማጠናከር ላይ የላቀ ተሳትፎ እንደሚያደርጉም መናገራቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።