ሐረሪ፣ ግንቦት 11/2013 (ዋልታ) – የሸዋልኢድ በዓል በሐረሪ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ በድምቀት ይከበራል፡፡
የሐረሪ ብሄረሰብ በአመት ከ26 የሚበልጡ በአላትን የሚከበርበት ሲሆን የሸዋልኢድ በአል አንዱ እና የመተጫጫ ልዩ ጊዜም ተደርጎ ይወሰዳል።
ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ሲከበር የቆየው ይህ በዓል በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራን እደሆነ ያሉት በሐረሪ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ሀላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን ገልጸዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል በዓሉን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ሀላፊው ገልፀዋል።
የሸዋልኢድ በአል ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በድምቀት ይከበራል።
(በቁምነገር አህመድ)