የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የማምረት አቅም እየተሻሻለና ምርቱን እየጨመረ መሆኑ ተገለፀ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የማምረት አቅሙን እያሻሻለና ምርቱን እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የማምረት አቅሙን በመጨመር የከተማዋን ነዋሪ ፍላጎት መሙላት እንደለበት አሳስበዋል።
ምክትል ከንቲባው በተሟላ ሁኔታ ምርቱን በአጭር ጊዜ ማሳደግ እንዳለበት ከፋብሪካው አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
ከሸገር ዳቦ ባሻገር ሁሉም የከተማዋ እንዱስትሪዎች የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርበት የሚያጋጥማቸውን ችግር ለምፍታት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አደም ኑሪ በበኩላቸው የሸገር ዳቦ ምርት በቀጥታ ለተጠቃሚ የሚደርስበትን አሰራርና የቁጥጥር ሂደት ንግድ ቢሮው ዝርዝር አሰራር ማውረዱን መግለጻቸውን የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!