የሽብርተኛው በህዳሴ ግድብ በኩል ተደጋጋሚ ማጥቃት ሙከራ አለመሳካት

ሌተናል ጀኔራል አስራት ዲኔሮ

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) ሽብርተኛው በህዳሴ ግድብ በኩል ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም በመከላከያ ሰራዊትና በክልሎች ልዩ ኃይል መደምሰሱን የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የመተከል የተቀናጀ ግብርኃይል ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዲኔሮ አረጋገጡ።

በዚህም ውጊያ ላይ ሽብርተኛው የተለያዩ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ፀረ-ተሽከርካሪና ፀረ ሰው ፈንጅዎችንና ተቀጣጣይ ቦንቦችን አስታጥቆ ቢልክም ሰራዊታችን ከክልሎች ልዩ ኃይል ጋር በመጣመር አኩሪ ገድል ፈጽመዋል ብለዋል፡፡

ሽብርተኛው የላካቸው ቅጥረኞች ከ220 በላይ ሲደመሰሱ ከ70 በላይ ቆስለውበት ቁስለኞችን ይዞ ወደ መጣበት ሸሽቷል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

አገራችን ያለችበትን ችግር የምትወጣው በህብረተሰቡ ድጋፍ ነውና ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ሲያይ ጥቆማ በመስጠት የጁንታውን ህልም በጋራ ማምከን አለብን ሲሉ አሳስበዋል።