የሽብር ቡድኑ ህወሃት የተከዜ ድልድይን ማውደሙ ተገለጸ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የሽብር ቡድኑ ህወሃት የእርዳታ መስመርን ለመገደብ ሆን ብሎ የተከዜ ድልድይን ማውደሙ ተገልጿል።

የትግራይ አርሶ አደሮች የመኸር ግብርና እንዲያከናውኑ ለመደገፍ የወጣውን የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ ያደረገው የሽብር ቡድኑ ህወሃት የተከዜ ድልድይን ሆን ብሎ ወደ ክልሉ የሚወስደውን የእርዳታ መስመር ለመገደብ ማውደሙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።