የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እጃቸውን እንዲሰጡ የተማረኩ የቡድኑ አባላት ጥሪ አቀረቡ

መስከረም 3/2015 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት ህጻናትን ጭምር ወደ ጦርነት እየማገደ በመሆኑ በአውደ ውጊያ የሚገኙ የትግራይ ወጣቶች እጃቸውን እንዲሰጡ በምዕራብ ግንባር የተማረኩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ጥሪ አቅርበዋል።

አሸባሪው ሕወሓት በምዕራብ ግንባር 11 ክፍለ ጦር እንዲሁም አሉኝ የሚላቸውን በርካታ ኮማንዶዎች ቢያሰልፍም ቡድኑ ሽንፈት መከናነቡ ተጠቁሟል።

ቡድኑ ከህጻናት እስከ አዛውንት በመመልመል ወደ ጦርነት ማሰለፉን ምርኮኞች ተናግረዋል።

ምርኮኞቹ ቡድኑ ያሰማራው ጦርም ሙት፣ ምርኮኛና ቁስለኛ መሆኑን ገልጸው እጃቸውን እንዲሰጡ ሲሉ ለትግራይ ወጣቶች ጥሪ አቅርበዋል።

ከተማረኩ በኋላ ለተደረገላቸው እንክብካቤ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ቆስለው የተማረኩትም ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ተስፋዬ አባተ (ከግንባር)