የሽብር ቡድኖቹን በደገፉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ምርመራ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) ለአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አዩብ አሕመድ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ጨምሮ ከደኅንነትና የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ሽብርተኞቹን ቡድኖች በገንዘብና በቁሳቁስ ይደግፋሉ የተባሉ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የተወሰኑት መለቀቃቸውንና ሌሎች መረጃና ማስረጃ ተገኝቶባቸው ምርመራው እንደቀጠለባቸው አስታውቀዋል።
7 ድርጅቶችም ታሽገው ምርምራ እየተደረገባቸው ሲሆን፤ 11 ተሸከርካሪዎች ደግሞ ሥራ እንዲያቆሙ መደረጉን ገልጸዋል።